በዛሬው ዕለት ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ እና የኢምባሲው ዲፕሎማቶች በእስራኤል ሉድ ከተማ በመገኘት Strauss Coffee በመባል የሚታወቀው በእስራኤል የቡና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጉልህ ድርሻ ያለው የማምረቻ ተቋም ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ድርጅቱ የሚረከባቸውን የቡና ዓይነቶች እና የአረካከብ ሂደት፣ የላብራቶሪ የጥራት ቁጥጥር እንዲሁም የቡና ምርት ማቀነባበሪያ በሚመለከት በድርጅቱ ኃላፊዎችና በዘርፉ ባለሙያዎች ገለፃ ተደርጓል።
ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ከ Mr. Zion Cohen የድርጅቱ የቴክኖሎጂ ክፍል ኃላፊ ጋር ባደረጉት ውይይት ኩባንያው የጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ቡና በእስራኤል ገበያ ያለው ድርሻ እንዲጨምር የሚያደርግ በመሆኑ የሚበረታታ ተግባር ነው በማለት፤ የአገራችንን ቡና ወደ እስራኤል በብዛት ለማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ምክክር አድርገዋል።በመጨረሻም ኢምባሲችን ከድርጅቱ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ቡና ማስተዋወቂያ መድረክ ለማዘጋጀት መግባባት ላይ ተደርሷል።
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram