ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በእስራኤል ቀጠናዊ ትብብር ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራል ከሆኑት Mr.Gilad Shadmon እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎችን ካካተተ ቡድን ጋር  ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢምባሲው ጽ/ቤት ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ኢትዮጵያ እና እስራኤል ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ፣ ኃይማኖታዊ እና የህዝብ ለህዝብ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል የሁለትዮሽ ትብብሩን በተለያዩ መስኮች ለማጠናከር እና ለማስፋት ፍላጎት መኖሩን ያብራሩት ክቡር አምባሳደር  ከእስራኤል ቀጣናዊ ትብብር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡ Mr.Gilad Shadmon በበኩላቸው መስሪያ ቤታቸው እስራኤል ከሌሎች አገሮች ጋር የምታካሄደውን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሰፋ የሚያስተባብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ህዝብ ለህዝብ፣ ተቋም ለተቋም እንዲሁም የእህትማማች ከተሞች ጉድኝት፣ በነጻ ትምህርት ዕድል፣ በኢኖቬሽንና ሌሎች መስኮች ትኩረት በመስጠት ድጋፍ እንደሚያደርግ አብራርተዋል፡፡ በተለያዩ ዘርፎች በኢትዮጵያ እና እስራኤል መካከል በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ያሉ አማራጮችን በመለየት የጋራ የአፈጻጸም መርሃ ግብር ለማዘጋጀት መግባባት ላይ  ተደርሷል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram