ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በሀገረ እስራኤል የኢፊዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾመው መምጣታቸውን ተከትሎ በእስራኤል ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመሃንዲሶች ቡድን አባላት ጋር ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ/ም ትውውቅና ውይይት አድርገዋል።

ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ከመሃንዲሶች ቡድን አባላት ጋር በመተዋወቃቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመሃንዲሶች ማህበር አባላት በአጠኑት ዘርፍ እና በተሰማሩበት ሙያ መስክ ለትውልድ አገራቸው በእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር በማድረግ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ስለሚያበረክቱበት እንዲሁም እስራኤል የቴክኖሎጅ አመንጭ አገር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ መሃንዲሶቹ ለአገራችን የሚጠቅምና ተፈላጊ የሆነ ቴክኖሎጅን ከማሸገጋገር አንጻር በእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር ላይ ድጋፍ በማድረግ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በመሃንዲሶቹ በኩልም ራሳቸውን በማስተዋወቅ የተሰማሩበትን ስራ መስክ፣ ልምድና ያጠኑትን ዘርፍ በዝርዝር ገልጸዋል። ክቡር አምባሳደር ተስፋዬን እንኳን ወደ እስራኤል በደህና መጡ በማለት በእስራኤል የሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን ተመኝተዋል። በተሰማሩበት ስራ መስክና በተማሩበት ሙያ ለትውልድ አገራቸው በእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር ልምዳቸውን በማካፈልና እውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር በማድረግ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። እንዲሁም በኢትዮጵያ ረዳት ለሌላቸው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ በባህርዳርና ጎንደር ዩኒቨርስቲዎች ስኮላርሽፕ ለመስጠት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ መሃንዲሶች በተሰማሩበት ስራ መስክና በአጠኑት ሙያ ለትውልድ አገራቸው በእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር የራሳቸውን ልምድ በማካፈል፣ እውቀትን በማሸጋገር ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀው ለተግባራዊነቱ በጋራና በቅርበት እንሰራለን ብለዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram