በእስራኤልና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም አገራችን በእስራኤል ያለውን የቡና፣ የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ገበያ እድል የበለጠ ለማስፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ፤ በአገራችን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተሻለ በልሁ የተመራ የቢዝነስ ልዑክ ከእስራኤል የቢዝነስ አካላት ጋር ተገናኝተው ውይይት አካሂደዋል። በመድረኩ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለዓለም ገበያ በሚያቀርባቸው የቡና፣ የቅባት እህሎችና ጥራጥሬዎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ እንዲሁም በሌሎች የግብርና ምርቶች ግልፀኝነት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የግብይት አሰራር ዘርግቶ የሚንቀሳቀስ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት መሆኑን በመጥቀስ፤ እስራኤል የአገራችንን የቅባት እህል ከሚገዙ አገሮች ቀዳሚ እንደሆነች ሁሉ፤ በቡና፣ በጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፎች ያለንን የገበያ እድል ማስፋት አስፈላጊ በመሆኑ፣ የእስራኤል ነጋዴዎች ከአገራችን ጋር የሚያደርጉትን የንግድ ግንኙነት እንዲያጠናክሩ እና አዳዲስ ነጋዴዎች በእነዚህ ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀርቧል።

ተሳታፊ አካላት በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት የተሻለ የምርት ጥራት ያላት መሆኑንና ከአገራችን ጋር ያላቸውን የንግድ ግንኙነት ማሳደግ እንደሚፈልጉ ገልፀው፣ ለንግድ ሥራው እንቅፋት ናቸው ያሉትን ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን፤ ለተነሱ ጥያቄዎች በልዑካን ቡድኑ ምላሽ ተሰጥቷል። በመጨረሻም ተሳታፊ አካላት እና ልዑካን ቡድኑ የአንድለአንድ ምክክር አድርገዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram