May 8, 2023
በእስራኤል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕከተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራልና የኢኮኖሚ ዲቪዥን ኃላፊ ከሆኑት Amb. Leo Vinovezky እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክተር Mr. Yehuda Avivi ጋር ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት አካሄደዋል፡፡
በውይይቱም እስራኤል እና ኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ከማጠናከር አንጻር በተለይ በኢኮኖሚ ዘርፍ እና በተለያዩ መስኮች ኤምባሲውና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበለጠ ትኩረት ሰጥተው በጋራ ለመስራት እና በየወቅቱ በመገናኘት በወቅታዊ የንግድ፣ኢንቨስትመንት፣ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ነክ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram