በእስራኤል ቴላ አቪቭ “Cleantech 2023” እና “Agromashov 2023” በሚል ስያሜ ዓለምአቀፍ ኤግዚብሽን እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ ኤግዚብሽን በኢምባሲያችን በኩል ተሳትፎ የተደረገ ሲሆን፤ ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በመርሀግብሩ አዘጋጆች በተዘጋጀው የቴሌቪዥን ጣቢያ (TV Studio) በመገኘት ቃለ-ምልልስ አድርገዋል። በቃለ-ምልልሳቸው በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር፣ ስለአገራችን የኢንቨስትመንት እድሎች በተለይም የግብርና ዘርፍ አማራጮች በሚመለከት ገለጻ በማድረግ፤ የእስራኤል ባለሃብቶች በአገራችን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ክቡር አምባሳደሩ ከመርሀግብሩ ጎን ለጎን የኤግዚብሽኑን የመክፈቻ ንግግር ካደረጉት የእስራኤል የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር Mr. Avi Dichter እንዲሁም የእስራኤል ዓለምአቀፍ የልማት ትብብር (ማሻቭ) ዋና ኃላፊ አምባሳደር ኢናት ሸሌይን በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ የተነጋገሩ ሲሆን፤ ለወደፊት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በሰፊው ለመመካከር መግባባት ላይ ተደርሷል።