ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ከእስራኤል የላኪዎች እና ዓለም ዓቀፍ ንግድ ትብብር ተቋም (Israeli Export and International Cooperation Institution) ጽ/ቤት በመገኘት በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ከተቋሙ የዓለምአቀፍ የቢዝነስ ጉዳዮች ም/ዳይሬክተር ጄኔራል ሳቢን ሴጋል (Sabine Segal) ጋር ዛሬ ነሐሴ 03 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ የእስራኤል የላኪዎች እና ዓለም ዓቀፍ ንግድ ትብብር እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ የቢዝነስ እንቅስቃሴ በሚመለከት Sabine Segal ገለጻ አድርገዋል። በገለጻቸው ወቅት ኢትዮጵያ ካላት ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ አማራጮች አንጻር ለእስራኤል ጠቃሚ አገር መሆኗን በመጥቀስ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደር ተስፋዬ በበኩላቸው ተቋሙ እያደረገ ያለውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ አገራችን ካላት ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንትና የንግድ አማራጮች አንጻር ከአገራችን ጋር ማስተሳሰር ጠቃሚ በመሆኑ፤ በተቋሙ ስር ያሉ ኩባንያዎች በአገራችን በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም ከተቋሙ ጋር በመተባበር ከተቋሙ ሥር ላሉ ኩባንያዎችና ለሌሎች የእስራኤል ባለሃብቶች የአገራችን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ዕድሎችን ለማስተዋወቅ የሚያግዝ መርሃ-ግብር በጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. ለማዘጋጀት መግባባት ላይ ተደርሷል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram