በእስራኤል የBeilinson Hospital ራቢን የህክምና ማዕከል የሕክምና ቡድን አባላት በኢምባሲያችን ተገኝተው ከክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ የሕክምና ቡድኑ እ.ኤ.አ ጁላይ 23 ቀን 2023 ጀምሮ ወደአገራችን በመሄድ ለአንድ ሳምንት ያህል ቆይታ በማድረግ በጎንደር እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች የቀዶ ጥገና የሕክምና አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን የሕክምና ድጋፍ እንዲሁም ለሕክምና ባለሙያዎች የሙያ ስልጠና እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።  ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ በበኩላቸው ቡድኑ ስለሚያደርገው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አመስግነው ለተልዕኮው መሳካት ኢምባሲው አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram