ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የተውጣጣ የልዑካን ቡድን በእስራኤል ከሚኖሩ-ቤተ እስራኤላዊያን ኮሚኒቲዎች፣ መሪዎችና ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ጋር በሀምሌ 2 ቀን 2015 ዓ/ም ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይት ወቅት ተሳታፊዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችና በሀገራዊ ፕሮጀክቶች ለመሳተፍና ከዚህ ቀደም ሲያድርጉ የነበረውን ተሳትፎና ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ በቀረበው ውይይት መነሻ ጽሁፍ ሰፊ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን ከተሳታፊዎች በቀረቡ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በእስራኤል የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህና በልዑካን ቡድን አባላት ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በእስራኤል ሀገር ነዋሪ ነዋሪ የሆኑ ቤተ እስራኤላዊያን ወጣቶች በቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ የተሰማራ METEKU AI ኩባንያ አመራርና አባላት ጋር በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከልዑካን ቡድኑ አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram