በእስራኤል ከሚገኙ ባለሃብቶች እና የተለያዩ ኩባንያ ኃላፊዎች ከእስራኤል ኤክስፖርት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጮች ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ዛሬ ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ተካሂዷል።
በመድረኩ ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ አገራችን በግብርና፣ በአግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በማዕድን ማምረት እና በጤና ዘርፎች ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ መንግስት ለኢንቨስትመንት ከሰጠው ትኩረት አኳያ በዘርፉ ያሉ ማበረታቻዎች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለያዩ የልማት ኮሪደሮች መገንባታቸውንም አክለው አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም ባለሃብቶቹ እና ኩባንያዎች በአገራችን በተለያዩ ኢንቨስትመንት ዘርፎች የተመቻቸውን ሁኔታ በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ባለሃብቶቹ ከግንቦት 1-5 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገራችን በሚካሄደው “ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ” ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ባለሃብቶቹ በመድረኩ ላነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ክቡር አምባባሳደር ምላሽ የሰጡ ሲሆን በተናጥል ብሎም በሽርክና በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው ባለሃብቶች ጋር ወደፊትም በተናጠል ውይይት በማድረግ ኢምባሲው እንደየጉዳዩ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram