19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ’’ በሚል መሪ ሃሳብ በእስራኤል የሚገኙ የኃይማኖት አባቶች፣ኢትዮጵያውያን፣ ቤተ-እስራኤላውያን እና የኤምባሲው ባልደረቦች በተገኙበት  ዛሬ ሕዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በቴል አቪቭ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ተከብሯል።

 በዕለቱ ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በእስራኤል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕከተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በዓሉን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ እና ዕለቱን የሚመለከት መልዕክት አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ‘ኅብረ ብሔራዊ ፌዴራል ስርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቹ እና የመፍትሄ ሃሳቦቹ’ በሚል ርዕስ በሚሲዮኑ  ምክትል መሪ በክቡር አቶ ቤኩማ መርዳሳ ገለጻ ቀርቧል። በቀረበው ገለጻ ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየቶች እና ጥያያቄዎች ቀርበዋል። በቀረቡት ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ላይ በክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ሰፊ ማብራሪያ እና ገለጻ ጠሰጥቷል። በተጨማሪም ክቡር አምባሳደር በሰጡት ማጠቃለያ በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ቤተ- እስራኤላውያን በሀገራችን ብሔራዊ መግባባት እና የምክክር ባህል እንዲጎለብት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በዕለቱ ለበዓሉ የተዘጋጀ የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት በጋራ ተከናውኗል።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram