የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ‘’የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና’’ በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሕዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በቴል አቪቭ የኢፌዲሪ ኤምባሲ የፓርቲው አባላት፣ደጋፊዎችና የኤምባሲው ባልደረቦች በተገኙበት ተከብሯል።
በዕለቱ ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕከተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በዓሉን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ‘’የህልም ጉልበት፤ለዕምርታዊ ዕድገት!!’’ በሚል ርዕስ በምክትል የሚሲዮኑ መሪ በክቡር አቶ ቤኩማ መርዳሳ ሰፊ ገለጻ ቀርቧል። በገለጻው ፓርቲው ከተመሰረተ ጀምሮ የተገኙ ቱርፋቶች፣ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎች በዝርዝር ቀርበዋል። በቀርበው ገለጻ በተሳታፊዎች ሃሳብ ከተሰጠ በኋላ ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በሰጡት ማጠቃለያ የአገራችን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥና አገራዊ ህልማችን እውን ለማድረግ የፓርቲው አባላት፣ደጋፊዎች፣ሰራተኞችና መላው ህዝብ የራሱን ሚና ሳያሳንስ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ለበዓሉ የተዘጋጀ የሻማ ማብራትና የዳቦ ቆረሳ ሥነ ስርዓትም በአባላትና በደጋፊዎች በጋራ ተከናውኗል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram