በእስራኤል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለእስራኤል ፕሬዝዳንት H.E. Mr. Isaac Herzog በፕሬዝዳንቱት ጽ/ቤት በመገኘት አቀረቡ።
ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበራቸው ውይይት በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ያለውን ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በተለያዩ መስኮች ለማስፋት እንደሚሰሩ ገልጻዋል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ኢትዮጵያ ግድቡን ለልማት ዓላማ እየገደበች መሆኑን፣ በፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም እንደምታምን እና በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተጀመረው የሶስትዮሽ ድርድር ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሄ እንደሚያስገኝ እምነት እንዳላት ገልፀው፤ ሆኖም የአረብ ሊግ በየጊዜው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚያወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ከዚህ በተጫማሪም በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ባለው የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ ላይ የኢትዮጵያን ሚና በሚመለከት ተነጋግረዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ታሪካዊ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በእስራኤል ልዩ ቦታ እንዳለው እና አምባሰደሩ በቆይታቸው ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸው፤ አምባሳደሩ በእስራኤል አገር በሚኖራቸው ቆይታ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉላቸው ቃል ገብተዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram