ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት“ በሚል መሪ ቃል ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢምባሲው ጽ/ቤት ተከበሯል፡፡
በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ላይ በእስራኤል ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአገራችን ብዝኃነትን እና ህብረ- ብሔራዊነት በህገ መንግስት የፀናበት፣ በእኩልነት፣ በወንድማማችነት እና በመቻቻል አገረ-መንግስት የሚገነባበት የአንድነታችን ምልክት የሆነ ዕለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዓለም ላይ የፌዴራል ስርዓት የሚከተሉ አገሮችንና ተሞክሯቸውን በማንሳት የፌዴራሊዝምን ፅንሰ ሃሳብ አብራርተዋል፡፡ ከዚህ አኳያ አገራችን የምትከተለው የፌዴራሊዝም ስርዓት ለብዝኃነት እና ህብረ-ብሔራዊ አንድነት መተግበር ትክክለኛ የመንግስታችን አወቃቀር ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡በስነ-ስርዓቱ ላይ የሚሲዮኑ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን የዳቦ ቆረሳ እና ዕለቱን የሚያደምቅ ሻማ በማብራት ስነ-ስርዓት በማከናወን ተከብሯል፡፡