ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሀይ የተመራ እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ያካተተ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢምባሲው ጽ/ቤት ውይይት አካሄዱ። በወቅቱም ክቡር አምባሳደር ጎንደር እና ሪሾን ለጽዮን ከተሞች የእህትማማችነት ጉድኝት የመግባቢያ ስምምነት በ1998 ዓ.ም. ተፈራርመው በከንቲባዎች ደረጃ የጉብኝት ልውውጥ በማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን አስታውሰው ጎንደር ካላት ሰፊ የቱሪዝም መስህቦች አኳያ በዘርፉ አተኩሮ ቢሰራ የበለጠ ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል ገልጸዋል። ከጎንደር አከባቢ የመጡ በርካታ ቤተ-እስራኤላውያን በእስራኤል በተለያዩ አከባቢዎች መኖራቸው  ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ትስስር ያላቸው መሆኑ ቱሪዝምን ለማስፋፋት እንደመልካም አጋጣሚ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። በከተማ ንጽህና እና አመራር፣ በተቋማት ለተቋማት ትብብር እና በሌሎች የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት በማድረግ የሁለቱን ከተሞች የጋራ ተጠቃሚነት ማስፋት እንደሚቻል ክቡር አምባሳደር አክለው ገልጸዋል። 

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ በበኩላቸው በብዙ መስኮች ትብብሩ ለማስፋት እንዲቻል የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከሪሾን ለጽዮን ከተማ የስራ ኃላፊዎች የጉብኝት ልውውጥ ማካሄዱን ጠቁመው የጎንደር ከተማ በቱሪዝም፣ በትምህርት፣ በጤና እና የከተማዋን ሁለንተናዊ ልማት እና ጊዜውን የሚመጥን ደረጃ ላይ ለማድረስ የሚያስችል ልምድ እና ቴክኖሎጂ ከሪሾን ለጽዮን ከተማ መቅሰም እንዲምትፈልግ፤ ይህን  ለማሳከት ከኢምባሲው ጋር በቅርበት ለማስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ከቡር አምባሳደር እና ከንቲባው በጎንደር እና ሪሾን ከተሞች መካከል የተመሰረተውን የእህትማማች ከተሞች ጉድኝት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ተካሂዷል ።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram