በኢንቨስትመንት መስክ ከተሠማሩት የእስራኤል ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ሜትሬሊ የተባለው ኩባንያ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በተለይም በኢንቨስትመንት እንዲሁም የበጎ አድራጎት ሥራዎችን፣ በአፍሪካ እና በእስራኤል መካከል ያለውን ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲሁም የቢዝነስ አማራጮች በሚመለከት ባዘጋጀው መድረክ ገለፃ ያቀረበ ሲሆን፤ በዚህም የተለያዩ አካላት ተሳትፈዋል።  

በመድረኩ ክቡር አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከተለያዩ የእስራኤል ባለሃብቶች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የጎንዮሽ ስለአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና ስለኢንቨስትመነት እድሎች ውይይት አድርገዋል። በዚህ ወቅት የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና የቢዝነስ ድርጅት ተወካዮች በአገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የተፈረመ የሰላም ስምምነት የሚደነቅ መሆኑን እንዲሁም በአገራችን ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመገንዘብ በአገራችን ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።  

አምባሳደር ረታ ከሜትሬሊ ኩባንያ መሥራችና ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሚ/ር ሃይም ታኢብ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ሜትሬሊ ኩባንያ አገራችን ቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች መካከል በግብርና እና ዘመናዊ መኖርያ ቤቶች ግንባታ ለመሠማራት ያለውን ፍላጎትአድንቀው፤ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ፕሮጀክቱ በአገራችን ተግባራዊ እንዲሆን ኢምባሲያችን ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ ገልፀዋል። 

ሚ/ር ሃይም በበኩላቸው ኩባንያው በአፍሪካ በሰባት አገራት እያደረገ ያለውን ውጤታማ ተግባር በመጥቀስ፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ለመጀመር ጥናት በማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን፣ ሆኖም በኮሮና ወረርሽኝ እና በተለያዩ ምክንያቶች በእንጥልጥል ላይ የቆየ መሆኑን አስታውሰው፤ አሁን ላይ ሥራ ለመጀመር ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልፀዋል።  

AmharicEnglishHebrew

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram