የእስራኤል እና የደቡብ ኮርያ 60ኛ ዓመት ወዳጅነት በማስመልከት በዓለምአቀፍ ወጣቶች ፌዴሬሽን (IYF) በተዘጋጀው የአምባሳደሮች መርሃ-ግብር በእስራኤል የሚገኙ የተለያዩ አገሮች የሚስዮን መሪዎችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።

በዚህ መድረክ በክብር እንግድነት የተጋበዙት በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ ክቡር አምባሳደር ረታ ዓለሙ ባደረጉት ንግግር “ለሁለቱ አገሮች ሕዝብና መንግስት የእንኳን አደረሳችሁ በማለት፤ በዘመናችን በዓለም ላይ በርካታ ተግዳሮቶች ቢከሰቱም፤ በአንፃሩ ተስፋ ሰጪ አጋጣሚዎች ያለ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዲፕሎማሲ መስክ ወዳጅነትና ትብብር ለማጠናከር ራዕይ ሰንቶ መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን” አስታውቀዋል። አክለውም ይህ የወጣቶች ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት አዲስ አስተሳሰብ እንዲጎለብት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል። አያይዘውም ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የደረሰባትን ጫና በመቋቋም፤ በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና ማሕበራዊ ለውጦችን እንዳስመዘገበች በዝርዝር አስረድተዋል።

 

AmharicEnglishHebrew

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram