ኢምባሲያችን በእስራኤል ከሚገኘው ኦኖ አካዳሚ ኮሌጅ ጋር በመተባበር “ኢትዮጵያ በእየሩሳሌም” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ወዳጅነት ለማጠናከር የሚያግዝ ዐውደ ጥናት ተጀምሯል ። በዚህ መርሐ ግብር በተለይ የሁለቱን አገሮች የሚያስተሳስሩ የቤተ እስራኤል ማኅበረሰብ ታሪክ በትክክል ለመረዳት፣ እንዲሁም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ደብረ ሥልጣን ገዳም (ዴር ሡልጣን) ጨምሮ በባለቤትነት ያላትን ይዞታዎች መብታችን ለማስጠበቅ የሚያግዝ መሆኑን የዐውደ-ጥናቱ ዋና አስተባባሪ ራቭ ዶ/ር ሻሮን ሻሎም ተናግረዋል ።

በመክፈቻው ንግግር ያደረጉት ክቡር አምባሳደር ረታ ዓለሙ ሁለቱ አገራት በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ያለው ትብብር እንዲጠናከር ለማድረግ በምሁራን ደረጃ ዓውደ ጥናት ማዘጋጀት እና ማቅረብ መቻሉ ትልቅ ውጤት ነው፣ ብለዋል። በማያያዝም ምሁራኑ በተለያዩ ርዕስ ጉዳዮች የሚያቀርቡት ጥናትና የሚያደርጉት ምክክር የሁለቱን ታሪካዊ ወዳጅነትና የሕዝብ የሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ መሠረት ያለው ከመሆኑም በላይ ታሪካዊ ቅርስ ለትውልድ ለማተላለፍ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል።

ዓውደ ጥናቱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፤ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር ይደረግባቸዋል። በአገራችን በኩል የጎንደር ዩኒቨርስቲ ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ እና ሌሎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram