በእስራኤል Coffee Fest 2022 የተባለ ዓለምአቀፍ የቡና ዓውደ ርዕይ መስከረም 03 ቀን 2015 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ፣ በዚህ ወቅት የአገራችን ቡና የሚመለከት መርሃግብር ቀርቧል። በመርሃግብሩ መክፈቻ በኢምባሲያችን በኩል የአገራችን ቡና ለተሳታፊዎች በማቅረብ የኢትዮጵያ ቡና የማስተዋወቅ ሥራ ተሰርቷል።

ይህ የቡና ዐውደ ርዕይ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ኢምባሲያችን ከአገራችን የላኪዎች ማሕበር እና ከዐውደ ርዕዩ አዘጋጆች ጋር በጥምረት የአገራችን የዘርፍ ኩባንያዎች በመርሃግብሩ በመሳተፍ የአገራችን ቡና እያስተዋወቁ ሲሆን፣ ይህ ፌስቲቫል ከእስራኤል እንዲሁም ከተለያዩ አገራት ከመጡ ባለሃብቶች እና ኩባንዎች ጋር ምክክር ለማድረግና ትስስር ለመፍጠር ይስችላል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram